ዮሐንስ 17:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ፣ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝንም ክብሬን እንዲያዩ እፈልጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባት ሆይ፥ የሰጠኸኝ እነዚህ እኔ ባለሁበት አብረውኝ ይኖሩ ዘንድና የሰጠኸኝን ክብሬን ያዩ ዘንድ እወድዳለሁ፤ ዓለም ሳይፈጠር ወድደኸኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ። |
ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባርያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።
እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።
ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን የሆንነው፥ የቀረነውም ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።