ዮሐንስ 15:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በሕጋቸው ‘በከንቱ ጠሉኝ’ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም፣ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው፥ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በኦሪታቸው፦ በከንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በሕጋቸው፦ “በከንቱ ጠሉኝ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። |
ከዚያም “ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ይገባዋል ብዬ የነገርኋችሁ ቃል ይህ ነው፤” አላቸው።
ስለ ሁላችሁም አይደለም የምናገረው፤ እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ቅዱስ መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤
ከእናንተ ዘንድ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆንበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ የማንንም ሰው እንጀራ እንዲያው በነፃ አልበላንም።