ነገር ግን የእስራኤል ቤት እኔን መስማት እንቢ ብለዋልና አንተንም አይሰሙህም፥ ምክንያቱም የእስራኤል ቤት ሁሉ የጠነከረ ግምባርና የደነደነ ልብ አላቸውና።
ዮሐንስ 15:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ባርያ ከጌታው አይበልጥም፤’ ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን ካሳደዱኝ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌንም ከጠበቁ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ባሪያ ከጌታው አይበልጥም’ ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን አሳድደውኝ ከሆነ፣ እናንተንም ያሳድዷችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነም ቃላችሁን ይጠብቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን አስታውሱ፤ እኔን ካሳደዱኝ እናንተንም ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ከጠበቁ ቃላችሁንም ይጠብቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ፦ ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ የለም ያልኋችሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳደዱ እናንተንም ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ቢሆንስ ቃላችሁንም በጠበቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባርያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው እንደ ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ። |
ነገር ግን የእስራኤል ቤት እኔን መስማት እንቢ ብለዋልና አንተንም አይሰሙህም፥ ምክንያቱም የእስራኤል ቤት ሁሉ የጠነከረ ግምባርና የደነደነ ልብ አላቸውና።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፦ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን በእስራኤል ላሉት ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት እንዲሆን ተሾሞአል፤
አይሁድ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም እንኳን ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም፤’ ትላለህ።