ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።
ዮሐንስ 15:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድቷደዱ የእኔ ትእዛዝ ይህች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። |
ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ አድጎአልና፥ የእናንተም የእያንዳንዳችሁ ሁሉ ፍቅር ለእርስ በርሳችሁ በዝቶአልና፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግዴታ አለብን፤
አሁንም እመቤት ሆይ! አዲስን ትእዛዝ አልጽፍልሽም ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረውን ነው፥ ይህም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ።