La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 11:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም እኅቶቹ “ጌታ ሆይ! እነሆ የምትወደው ታሞአል፤” ብለው ወደ እርሱ ላኩበት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኅትማማቾቹም፣ “ጌታ ሆይ፤ የምትወድደው ሰው ታምሟል” ብለው መልእክት ላኩበት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኅትማማቾቹም “ጌታ ሆይ፥ ያ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ ኢየሱስ ላኩበት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ እኅቶቹ “ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ እርሱ ላኩ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 11:3
16 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም፥ “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፥ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋልኝ” አለው።


ደስታዬ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው።


ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፦ “አታልቅሽ፤” አላት።


አንድ ሰው ታሞ ነበር፤ እርሱም እንደ ማርያምና እንደ እኅትዋ ማርታ ከቢታንያ የነበረው አልዓዛር ነው።


ይህንንም ከተናገረ በኋላ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ፤” አላቸው።


ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጉርዋ ያበሰችው ስትሆን፤ የታመመውም አልዓዛር ወንድምዋ ነበር።


ማርታም ኢየሱስን “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር፤


ስለዚህም አይሁድ “እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ፤” አሉ።


ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን እንዲሁም አልዓዛርን ይወድ ነበር።


እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ ስለሆንኩም መልካም ትናገራላችሁ።


ከደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ ይወደው የነበረው አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤


ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፤ ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውኩት።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።