ደግመኛም ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም አምልጦ ሄደ።
እንደ ገናም ሊይዙት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከእጃቸው አመለጠ።
እነርሱም እንደገና ሊይዙት ፈለጉ፤ እርሱ ግን ከእጃቸው አምልጦ ሄደ።
ዳግመኛም ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም አመለጠ።
እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ።
ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ተማከሩ።
አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም።
ከእነርሱም አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን እጁን ማንም አልጫነበትም።
ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረባቸው፥ ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።