ዮሐንስ 10:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በበሩ የሚገባ ግን እርሱ የበጎቹ እረኛ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። |
እርሱም የቀደመውን ዘመን እንዲህ ብሎ አሰበ፦ የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለው? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለው?
የአሦርን ምድር በሰይፍ፥ የናምሩድንም ምድር በመግቢያው ይጠብቃሉ፤ ወደ ምድራችን በገባ ጊዜ፥ ዳርቻችንንም በረገጠ ጊዜ ከአሦር ይታደገናል።
የገዙአቸው ያርዱአቸዋል፥ እንደ በደለኞች አይቆጠሩም፥ የሸጧቸውም፦ “ባለ ጠጋ ሆኛለሁ፤ ጌታ ይመስገን!” ይላሉ። እረኞቻቸው እንኳን አይራሩላቸውም።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።”