ኢዮብ 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፥ ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤ ምሰሶዎቿንም ያንቀጠቅጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ምድርን ከቦታዋ ያንቀጠቅጣል፤ ምሰሶችዋንም ያነቃንቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርን ከሰማይ በታች ከመሠረቷ ያናውጣታል፥ ምሰሶዎችዋም ይንቀጠቀጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፥ ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ። |
ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።
ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።
ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።