ኢዮብ 9:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ፣ ለመንጠቅ ቍልቍል እንደሚበርር ንስር ይፈጥናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ ይሮጣሉ፤ እንደ ነጣቂ ንስርም ይፈጥናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመርከብ መንገድ ፍለጋ፥ ወይም የሚበርና የሚበላውን የሚፈልግ የንስር ፍለጋ እንደማይታወቅ ሕይወቴ እንዲሁ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋል። |
መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ወደ ሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ወደሆነና ወደሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።
ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኩላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፥ ለመንጠቅ እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ።