ኢዮብ 6:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እናንተ እንደዚሁ ሆናችኋል፥ መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እናንተ እንደዚያ ሆናችሁብኝ፤ መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም ለእኔ እንደ እነዚያ ደረቅ ወንዞች ናቸሁ። የደረሰብኝን መከራ አይታችሁ ወደ ኋላ አፈገፈጋችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እናንተ ያለ ምሕረት መጣችሁ፤ ቍስሌንም አይታችሁ ፈራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እናንተ እንደዚሁ ሆናችኋል፥ መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ። |
ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ ተብሎ ተጽፎአልና፥ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤