ኢዮብ 6:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቴማን ነጋዴዎች ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተጠባበቁአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉ፤ የሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቴማ መንገደኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤ የሳባ ነጋዴዎችም ውሃ ለማግኘት ተስፋ ያደርጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቴማናውያንን መንገዶች፥ የሳባውያንን ክፋትና ቸልተኝነት ተመልከቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቴማን ነጋዴዎች ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተጠባበቁአቸው። |
ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።