ጉልበቴ የድንጋይ ጉልበት ነውን? ሥጋዬስ ነሐስ ነውን?
የድንጋይ ጕልበት አለኝን? ሥጋዬስ ናስ ነውን?
እኔ እንደ ድንጋይ ጠንካራ ነኝን? ሰውነቴስ እንደ ናስ ጠንካራ ነውን?
ጕልበቴ የድንጋይ ጉልበት ነውን? በውኑ ሥጋዬስ እንደ ናስ ነውን?
ጕልበቴ የድንጋይ ጕልበት ነውን? ሥጋዬስ እንደ ናስ ነውን?
“ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!
አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው፥ አካላቱ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው።
በስተ ኋላው ብሩህ መንገድን ያበራል፥ ቀላዩም ሽበት ይመስላል።
እጠብቅ ዘንድ ጉልበቴ ምንድነው? እታገሥም ዘንድ ፍጻሜዬ ምንድነው?
በውኑ ረድኤት በእኔ እንደሌለ ጥበብም ሁሉ ከእኔ ዘንድ እንደ ተባረረ አይደለምን?”