ኢዮብ 5:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘርህም እንደሚበዛ፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር ብዙ እንደሚሆን ታውቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሮችህ አያሌ እንደሚሆኑ፣ የምትወልዳቸውም እንደ ሣር እንደሚበዙ ታውቃለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትውልድህ እንደሚበዛ ታውቃለህ፤ ዘርህም እንደ መስክ ሣር ይበዛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘርህም ብዙ እንዲሆን፥ ልጆችህም እንደ አማረ መስክ ሣር እንዲሆኑ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘርህም ታላቅ እንዲሆን፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር እንዲሆን ታውቃለህ። |
በምድር ላይ እህሉ ይትረፍረፍ፥ በተራሮችም ላይ ሰብል ይወዛወዝ፥ ፍሬውም እንደ ሊባኖስ ከፍ ከፍ ይበል፥ ሰዎችም በከተማ እንደ ምድር ሣር ይለምልሙ።