ኢዮብ 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁንም ተጣራ፥ የሚመልስልህ አለን? ከቅዱሳንስ ወደማናቸው ትዞራለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስኪ ተጣራ፤ የሚመልስልህ አለን? ከቅዱሳንስ ወደ ማንኛው ዘወር ትላለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! መልስ የሚሰጥህ ሰው ብታገኝ እስቲ ተጣራ፤ ርዳታ ይሰጥህ ዘንድ ከመላእክቱ ወደ ማንኛው ትመለከታለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሁንም የሚመልስልህ ካለ ጥራ፥ ከቅዱሳን መላእክትም የምታየው ካለ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ጥራ፥ የሚመልስልህ አለን? ከቅዱሳንስ ወደማናቸው ትዞራለህ? |
እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።