ኢዮብ 41:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዱላን እንደ ገለባ ይቈጥረዋል፥ ሰይፎች ሲንቀጠቀጡ ይስቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤ የእሳትም ነበልባል ከአፉ ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የትንፋሹ ግለት ከሰል ያቀጣጥላል፤ የእሳት ነበልባልም ከአፉ ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መኝታው እንደ ስለታም ድንጋይ ነው፤ የባሕር ወርቅ ሁሉ በእርሱ ዘንድ እንደማይቈጠር ጭቃ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሎታውን እንደ ገለባ ይቈጥረዋል፥ ሰላጢኑም ሲሰበቅ ይስቃል። |
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።