ኢዮብ 40:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ አውራ ነው፥ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤ በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ከፈጠርኳቸው ፍጥረቶች ሁሉ ኀያል ከእኔ በቀር የሚያሸንፈው የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ የእግዚአብሔር የፍጥረቱ አውራ ነው። ከተፈጠረም በኋላ መላእክት ሣቁበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው፥ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው። |
በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።