ኢዮብ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር ትቀየማለህን? ቃልንስ ከመናገር ማን ሊቀር ይችላል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ከአንተ ጋራ ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን? ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! አንድ ሰው ደፍሮ ቢናገርህ በትዕግሥት ታዳምጣለህን? ነገር ግን ከመናገር ማን ይቈጠባል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመከራ ሳለህ ነገር አታብዛ፥ የነገር ብዛት ምን ይጠቅምሃል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰው ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ ቢሞክር ትቀይማለህን? ቃልንስ ከመናገር ሊቀር የሚችል ማን ነው? |
እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።
ስለዚህ በጌታ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤ ከመታገሥ ደክሜአለሁ፤ “በጎዳና ባሉ ሕፃናት ላይ በጉልማሶችም ጉባዔ ላይ በአንድነት አፍስሰው፤ ደግሞም ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም በእድሜአቸው ከገፉት ጋር ይያዛሉና።