ኢዮብ 39:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐሽ ሊያገለግልህ ፈቃደኛ ነውን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? በበረትህስ አጠገብ ያድራልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጎሽ የተባለው የዱር እንስሳ አንተን ለማገልገል ፈቃደኛ ይሆናልን? በበረትህስ ውስጥ ሊያድር ይችላልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጎሽ ያገለግልህ ዘንድ ይፈቅዳልን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? |
ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”