በእርሱ ላይ የፍላጻ ኮረጆ፥ የሚብለጨልጭ ጦርና ሰላጢን ያንኳኳሉ።
ከሚብረቀረቀው ጦርና ዐንካሴ ጋራ፣ የፍላጻው ኰረጆ ጐኑ ላይ ይንኳኳል።
የሚጋልቡአቸው ጦረኞች የያዙአቸው የጦር መሣሪያዎች በፀሐይ እየተብለጨለጩ እርስ በርሳቸው ሲፋጩ ይሰማል።
ቀስትና ጦር በእርሱ ላይ ይበረታሉ፥
በእርሱ ላይ የፍላጻ ኮረጆና ብልጭልጭ የሚል ጦር ሰላጢንም ያንኳኳሉ።
በፍርሃት ላይ ይስቃል፥ በጭራሽ አይደነግጥም፥ ሰይፍም አያሸሸውም።
በነውጥና በቁጣ መሬትን ይውጣል፥ የመለከትም ድምፅ ቢሰማ አይቆምም።
ጌታ የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል፤ አጥፊዎች አጥፍተዋቸዋልና፥ የወይናቸውን ቅርንጫፎች አጥፍተዋልና።