ኢዮብ 38:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርንስ በስፋትዋ አስተውለሃታልን? ሁሉን አውቀህ እንደሆነ ተናገር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድርን ስፋት ታውቃለህን? ይህን ሁሉ ዐውቀህ ከሆነ፣ ንገረኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓለም ምን ያኽል ትልቅ እንደ ሆነች ማወቅ ትችላለህን? እስቲ ይህን ሁሉ ታውቅ እንደ ሆነ ንገረኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰማይ በታች ያለ የምድርንስ ስፋት አስተውለሃልን? መጠኑም ምን ያህል እንደ ሆነ እስኪ ንገረኝ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርንስ በስፋትዋ አስተውለሃታልን? ሁሉን አውቀህ እንደ ሆነ ተናገር። |
ወደ ዳርቻው ትነዳው ዘንድ፥ ወደ ቤቱም የሚያደርሰውን ጐዳና ታውቅ ዘንድ፥ የብርሃን መኖሪያ መንገድ የት ነው? የጨለማውስ ቦታ ወዴት አለ?
ጌታ እንዲህ ይላል፦ በላይ ያለው ሰማይ ቢለካ፥ በታችም ያለው የምድር መሠረት ቢመረመር፥ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ትውልድ በሙሉ እጥላለሁ፥ ይላል ጌታ።”