ኢዮብ 37:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበስተኋላው ድምፅ ያገሣል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጉዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤ በድምፁም ግርማ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁ በተሰማ ጊዜ፣ መብረቁን የሚከለክል የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስተኋላው ድምፅ ይጮኻል፤ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁም በተሰማ ጊዜ ሰዎች እንዲጠፉ አያደርግም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፥ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፥ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም። |