ኢዮብ 37:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብረቁንም ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ወደ ምድርም ዳርቻ ይሰድዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ሁሉ በታች ብርሃኑን ይለቅቃል፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ይልካል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መብረቁን ከሰማይ በታች ሁሉ ያሠራጫል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ድረስ ይልካል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል። |
ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤ የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፤ ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በቤተ በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።