እነሆ፥ በዙሪያው ብርሃኑን ይዘረጋል፥ የባሕሩንም ጥልቀት ይከድናል።
መብረቁን በዙሪያው እንዴት እንደሚበትን ተመልከት፤ የባሕሩንም ወለል ይሸፍናል።
እግዚአብሔር የባሕሩን ጥልቀት እየሸፈነ መብረቁን በዙሪያው እንዴት እንደሚበትን ተመልከት።
እነሆ፥ በዙሪያው ብርሃኑን ይዘረጋል የባሕሩንም ጥልቀት ይከድነዋል።
እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
የደመናውንም መዘርጋት፥ የማደሪያውንም ነጐድጓድ የሚያስተውል ማን ነው?
በእነዚህ በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፥ ብዙም ምግብ ይሰጣል።
ባድማውንና ውድማውን እንዲያጠግብ፥
ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ፥ ሰማይንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፥
የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ሄዱ፤ ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው ግድግዳ ሆነላቸው።
ውኆቹም ተመልሰው በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን ፈረሰኞችን የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደኑ፤ ከእነርሱም አንድ ስንኳ አልቀረም።
መብረቅ በርቆ ከሰማይ በታች ካለ አንድ ስፍራ ከሰማይ በታች ወዳለው ወደ ሌላ ስፍራ እንደሚያበራ፥ የሰው ልጅም፥ በቀኑ፥ እንዲህ ይሆናል።