በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ትዕቢት ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም።
ከዐመፀኞች ትዕቢት የተነሣ፣ ሰዎች ሲጮኹ አይመልስላቸውም፤
እነርሱ ይጮኻሉ እርሱ ግን ትዕቢተኞችና ክፉዎች ስለ ሆኑ መልስ አይሰጣቸውም።
በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ስድብ ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይሰማቸውም።
በውኑ መከራ በመጣበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋቸዋለሁ።
የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።
እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን።