Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 35:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በርግጥ እግዚአብሔር ከንቱ ጩኸታቸውን አይሰማም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ አያዳምጣቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በእርግጥ እግዚአብሔር ከልብ ያልሆነ ጩኸትን አይሰማም፤ ሁሉን የሚችል አምላክም አያተኲርበትም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት ክፉ ነገ​ርን ሊያይ አይ​ወ​ድም። እርሱ ሁሉን የሚ​ችል ዐዋቂ አም​ላክ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 35:13
20 Referencias Cruzadas  

ጌታ ከኀጥኣን ይርቃል፥ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሊያመልጡት የማይችሉትን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ፥ ወደ እኔም ይጮኻሉ፤ እኔም አልሰማቸውም።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


የምትለምኑትም ለፍትወታችሁ በማሰብ በክፉ ምኞት ስለሆነ፥ ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም።


“ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ የሚደጋገሙ ቃላትን አትጠቀሙ፥ እነርሱ ብዙ በመናገራቸው የሚሰሙ ይመስላቸዋልና።


የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለአንድነት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም።


በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፤ በእኔም ላይ ዓመፁ።


ሕግን ከመስማት ጆሮውን የሚመልስ ጸሎቱ እንኳን ሳይቀር አስጸያፊ ናት።


የኀጥኣን መሥዋዕት በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።


ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልመለስህልኝም፥ ተነሣሁ፥ ነገር ግን ዝም ብለህ ተመለከትኸኝ።


እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን።


ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን ዋጋው ከንቱ ነገር ይሆናልና።


የዚያን ጊዜ ወደ ጌታ ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም፤ በዚያን ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል፥ ሥራቸው ክፉ ነውና።


በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios