ኢዮብ 34:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እውነተኛ ብሆን እንደ ውሸተኛ ተቈጠርሁ፥ ምንም ባልበድል ቁስሌ የማይፈወስ ነው ብሏል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነተኛ ብሆንም፣ እንደ ውሸታም ተቈጥሬአለሁ፤ በደል ባይኖርብኝም፣ በማይፈወስ ቍስል ተመትቻለሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እውነተኛ ስሆን፥ እንደ ውሸተኛ ተቈጠርኩ፤ ምንም በደል ሳይኖርብኝ በማይፈወስ ቊስል እሠቃያለሁ’ ብሎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዴን ሐሰተኛ አደረገብኝ፤ በደልም ሳይኖርብኝ በግፍዕ መከራን እቀበላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምንም እውነተኛ ብሆን እንደ ውሸተኛ ተቈጠርሁ፥ ምንም ባልበድል ቍስሌ የማይፈወስ ነው ብሎአል። |
ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን?