ኢዮብ 34:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን፦ እኔ ሳልበድል ቅጣት ተቀበልሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማን ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ ‘እኔ በደለኛ ነኝ፤ ከእንግዲህ ግን አልበድልም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምናልባት አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ‘እስከ አሁን በድዬአለሁ ዳግመኛ አልበድልም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኀያሉ እግዚአብሔርን፦ እንዲህ የሚል አለ፥ እኔ በረከትን ተቀበልሁ፥ መያዣውንም አልወስድም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን፦ እኔ ሳልበድል ቅጣት ተቀበልሁ፥ |
አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ አንድም ሰው፦ ‘ምን አድርጌአለሁ?’ ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ጦርነትም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል።
እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥
በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና፥ ጉዳዬን እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን እስኪያደርግልኝ ድረስ የጌታን ቁጣ እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቁንም አያለሁ።
በለዓምም የጌታን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ ልትቃወመኝ መቆምክን አላወቅሁም፤ እንግዲህም ይህ አሁን በፊትህ ክፉ የሆነ ነገር ቢሆን እመለሳለሁ።”