ኢዮብ 34:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ፥ መኰንኖቹን፦ ክፉዎች ናችሁ ይላልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገሥታትን ‘ምናምንቴ ናችሁ፣’ መኳንንትንም፣ ‘ክፉዎች ናችሁ’ የሚላቸው እርሱ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡን የማትጠቅም ነህ፤ መኳንንቱንም ክፉዎች ናችሁ፤ የሚላቸው ማነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ የሚለው፥ መኳንንቱንም፦ ክፉዎች ናችሁ የሚላቸው ኀጢአተኛ ነው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ሰው ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ፥ መኳንንቱንም፦ ክፉዎች ናችሁ ይላልን? |
በዚያን ጊዜ ጳውሎስ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ! እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?” አለው።
ይልቁንም በርኩስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን፥ ጌትነትንም የሚንቁትን፤ ደፋሮችና እምቢተኞች ስለ ሆኑ ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይፈሩም፤