ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤
ኢዮብ 33:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋው እንደ ልጅ ሥጋ ይለመልማል፥ ወደ ወጣትነቱም ጊዜ ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ሥጋው እንደ ሕፃን ልጅ ገላ ይታደሳል፤ ወደ ወጣትነቱም ዘመን ይመለሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሥጋው እንደገና እንደ ልጅ ሥጋ ሆኖ ይታደሳል፤ እንደ ወጣትነቱም ጊዜ ይመለሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋውን እንደ ሕፃን ሥጋ ያለመልማል፤ ከሰዎችም ይልቅ ወደ ጕብዝናው ዘመን ይመልሰዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፥ ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል። |
ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤
በበኣሊም የበዓል ቀኖች ዕጣን ለእነርሱ በማጠንዋና ራስዋን በጉትቾችዋና በጌጥዋ በማስጌጥ ውሽሞችዋን ተከትላ እኔን በመርሳትዋ እቀጣታለሁ፥ ይላል ጌታ።