ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ጥበብ ለማግኘትም የሚመኙት እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
ኢዮብ 33:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕይወቱም እንጀራን፥ ነፍሱም ጣፋጭ መብልን ትጠላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያኔም ሕይወቱ መብልን ትጠላለች፤ ነፍሱም ምርጥ ምግብን ትጠየፋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ሕመምተኛው እህል መቅመስን ያስጠላዋል፤ ምርጥ የሆነ ምግብ እንኳ አያስደስተውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንኛውንም መብል መቅመስ አይችልም። ሰውነቱ ግን መብልን ትበላ ዘንድ ትመኛለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወቱም እንጀራን፥ ነፍሱም ጣፋጭ መብልን ትጠላለች። |
ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ጥበብ ለማግኘትም የሚመኙት እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።
እናንተም ድሀውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና፥ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም።