ኢዮብ 32:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ልብ በማድረግ ሰማኋችሁ፥ እነሆም፥ በእናንተ መካከል ኢዮብን ያስረዳ፥ ወይም ለቃሉ የመለሰ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሉ ልብ አደመጥኋችሁ፤ ነገር ግን ከእናንተ የኢዮብን ቃል ያስተባበለ ማንም የለም፤ ለንግግሩም አጸፋ የመለሰ አልተገኘም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥንቃቄ አደመጥኳችሁ፤ ሆኖም፥ ማንም ኢዮብን ለማስተባበል የቻለ የለም፤ ከእናንተም መካከል ለእርሱ ንግግር አጥጋቢ መልስ የሰጠ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ልብ አደረግሁ፤ እነሆም፥ ከእናንተ መካከል ኢዮብን የገሠጸ፥ ወይም ለተናገረው ቃልን የመለሰ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ልብ አደረግሁ፥ እነሆም፥ በእናንተ መካከል ኢዮብን ያስረዳ፥ ወይም ለቃሉ የመለሰ የለም። |