Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 32:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እናንተም፦ ጥበብን አግኝተናል፥ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አያሸንፈውም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ‘እኛ ጥበብ አግኝተናል፤ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ይርታው’ አትበሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለኢዮብ ተገቢ መልስ ሊሰጠው የሚችል እግዚአብሔር እንጂ ሰው ስላልሆነ፥ እናንተ ጥበብን አግኝተናል ብላችሁ በከንቱ አትመኩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እና​ን​ተም፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ አብ​ዝ​ተ​ና​ልም እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እናንተም፦ ጥበብን አግኝተናል፥ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አያሸንፈውም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 32:13
23 Referencias Cruzadas  

ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤


ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚህ ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው፥ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።


ኢየሱስም መልሶ “ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ኀጢአቱ የባሰ ነው” አለው።


ጌታም፥ የዳዊትን ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር፥ በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች በቅድሚያ ያድናል።


እነሆ፥ አንተ ከዳንኤል ይልቅ ጥበበኛ ነህ፥ ከአንተ የተሰወረ ምሥጢር የለም።


እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፦ “እነሆ፥ አስቀድሜ አውቄአቸዋለሁ” እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም።


ስለዚህ፥ አንተ፦ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፥ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር፥ ከመሆኑም በፊት አሳይቼህ ነበር።


ራሳቸውን እንደ ብልኅ ለሚቈጥሩ፤ በራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!


እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ራሩልኝ፥ ራሩልኝ፥ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና።


እንግዲህ እግዚአብሔር ጥፋተኛ እንዳደረገኝ፥ በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ።


“በእርግጥም እናንተ የሕዝብ ድምፅ ናችኋ! ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ!


ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል።


በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቁጣውም መንፈስ ያልቃሉ።


እርሱ ግን፦ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፥ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን?” አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።


እንዲህም አለ፦ “ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ ጌታ ሰጠ፥ ጌታ ወሰደ፥ የጌታ ስም የተባረከ ይሁን።”


ጌታም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።


አንተ፦ አብራምን ባለ ጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ፥ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።


በስንዴ ፋንታ አሜከላ፥ በገብስም ፋንታ ኩርንችት ይውጣብኝ።” የኢዮብ ቃል ተፈጸመ።


እንዲሁም ልብ በማድረግ ሰማኋችሁ፥ እነሆም፥ በእናንተ መካከል ኢዮብን ያስረዳ፥ ወይም ለቃሉ የመለሰ የለም።


እርሱ እኔን አይደለም የተናገረው፥ እኔም በእናንተ አነጋገር ዓይነት አልመልስለትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios