La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 31:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለነገሩማ ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባት ሆኜ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ መበለቲቱንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይልቁን ድኻ አደጉን ከታናሽነቴ ጀምሮ እንደ አባት አሳደግሁት፤ መበለቲቱንም ከተወለድሁ ጀምሮ መንገድ መራኋት፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ከወጣትነቴ ጀምሬ እንደ አባት ሆኜላቸዋለሁ፤ በሕይወቴ ዘመኔ ሁሉ ባልዋ የሞተባትን ረድቼአለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱን ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ እንደ አባቱ ከእ​ኔው ጋር አሳ​ድ​ጌው ነበር፤ ከእ​ና​ቱም ማኅ​ፀን ከተ​ወ​ለደ ጀምሮ አሳ​ደ​ግ​ሁት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱን ግን ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባቱ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ እርስዋንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፥

Ver Capítulo



ኢዮብ 31:18
8 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤


መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃቸዋል፥ የወላጅ አልቦችም ክንዶች ተሰብረዋል።


የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ወላጅ አልባውንና ረጂ የሌለውን አድኜ ነበርሁና።


ለድሀው አባት ነበርሁ፥ ለማላውቀውም ሰው ጠበቃ ነበርሁ።


እንጀራዬን ለብቻዬ በልቼ እንደሆነ፥ ወላጅ አልባውም ሳይደርሰው ቀርቶ እንደሆነ፥


ከልብስ እጦት የተነሣ አንድ ሰው ሲጠፋ አይቼ፥ ወይም ድሀ የሚሸፈንበት ሲያጣ ተመልክቼ፥


እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?