ኢዮብ 30:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥ እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ መሳርያ ሆነ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገናዬ ለሐዘን፣ እንቢልታዬም ለልቅሶ ተቃኝቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስታዬን እገልጥባቸው የነበሩት በገና እና እምቢልታ አሁን የሐዘን እንጒርጒሮዬ ማሰሚያ ሆነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ሕማሜ መሰንቆ፥ ልቅሶዬም በገና ሆነብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥ እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ ቃል ሆነ። |
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ጸጉር መላጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።