ኢዮብ 29:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዳቸውን መረጥሁ፥ እንደ አለቃ ሆኜ ተቀመጥሁ፥ ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር፥ ኀዘንተኞችን እንደሚያጽናና ኖርሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገድ መርጬላቸው አለቃቸው ሆኜ ተቀመጥሁ፤ በሰራዊትም መካከል እንዳለ ንጉሥ ኖርሁ፤ ሐዘንተኞችንም እንደሚያጽናና ነበርሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እንደ ፈለግኹት አስተዳድራቸው ነበር፤ ሠራዊቱንም እንደሚመራ ንጉሥ እመራቸው ነበር፤ በሚያዝኑበትም ጊዜ አጽናናቸው ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዳቸውን መረመርሁ፤ እንደ አለቃም ሆኜ ተቀመጥሁ፤ ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር ኖርሁ፤ በሚያዝኑም ጊዜ በእኔ ይጽናኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዳቸውን መረጥሁ፥ እንደ አለቃ ሆኜ ተቀመጥሁ፥ ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር፥ ኅዘነተኞችን እንደሚያጽናና ኖርሁ። |
እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”
ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
የገለዓድ አለቆችም፥ “እንግዲህ አሁን ወደ አንተ መጥተናል፤ አሞናውያንን እንድንወጋ በል ተነሥና አብረን እንሂድ፤ በገለዓድ በምንኖረው በሁላችንም ላይ አለቃ ትሆናለህ” አሉት።