ኢዮብ 28:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያ ድንጋዮችዋ የሰንፔር መከማቻ ናቸው፥ የወርቅም ድቃቂ ይገኛል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰንፔር ከዐለቷ ይወጣል፤ ከዐፈሯም የወርቅ አንኳር ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰንፔር የተባለው ዕንቊ በድንጋዮችዋ ውስጥ ይገኛል፤ በዐፈርዋም ውስጥ ወርቅ ይገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋይዋ እንደ ሰንፔር፥ ወርቅዋም እንደ አፈር የሆነ መሬት አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋይዋ የሰንፔር ስፍራ ነው፥ የወርቅም ድቃቂ አለው። |
የከተማይቱም ቅጥር መሠረቶች በከበረ ድንጋይ ሁሉ ያጌጦ ነበር፤ የመጀመሪያው መሠረት ኢያሰጲድ፥ ሁለተኛው ሰንፔር፥ ሦስተኛው ኬልቄዶን፥ አራተኛው መረግድ፥