ኢዮብ 28:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው መንገድዋን አያውቅም፥ በሕያዋን አገር አትገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ዋጋዋን አያውቅም፤ በሕያዋንም ምድር አትገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጥበብ ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶች በሚኖሩባት ምድር አትገኝም፤ እውነተኛ ዋጋዋንም የሚያውቅ ሰው የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሟች ሰው መንገድዋን አያውቅም፤ በሰዎችም ዘንድ አትገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው መንገድዋን አያውቅም፥ በሕያዋን ምድር አትገኝም። |
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
ኤላምም በዚያ አለች ብዛትዋም ሁሉ በመቃብሯ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸበሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፥ ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።