ኢዮብ 25:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ በከፍታውም ሰላምን የሚያሰፍን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ገዥነትና ግርማ የእግዚአብሔር ናቸው፤ በሰማይም ከፍታ ሥርዐትን ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሥልጣንና መፈራት የእግዚአብሔር ነው፤ በላይኛው ግዛቱ በሰማይ ሰላምን ይመሠርታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጥንቱን መፈራት በእርሱ ዘንድ ያለ አይደለምን? በከፍታውም ሁሉን ነገር አድራጊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ በከፍታውም ሰላም አድራጊ ነው። |
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
እርሱ ብቻ አዳኛችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ክብር፥ ግርማ፥ ኃይልና ሥልጣን ከዘመናት ሁሉ በፊት፥ አሁንም እስከ ዘለዓለምም ድረስ ይሁን፤ አሜን።