ኢዮብ 24:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወላጅ አልባውን አህያ ይነዳሉ፥ የመበለቲቱን በሬ ለመያዣነት ይወስዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የድኻ አደጉን አህያ ቀምተው ይሄዳሉ፤ የመበለቲቱንም በሬ በመያዣነት ይወስዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የድኻ አደጉን አህያ ይቀማሉ፤ ባልዋ የሞተባትን ሴት ንብረት የሆነውንም በሬ፥ በመያዣ ስም ይወስዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድሃአደጎቹን አህያ ይነዳሉ የመበለቲቱንም በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የድሀ አድጎቹን አህያ ይነዳሉ፥ የመበለቲቱን በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ። |
“አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባርያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። በዚህ ዓይነት ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”