ኢዮብ 24:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቶቹን በጨለማ ይሰረስራሉ፥ በቀን ይሸሸጋሉ፥ ብርሃንም አያውቁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጨለማ፣ ቤት ሰርስረው ይገባሉ፤ በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንንም አይፈልጉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌቦች በሌሊት ቤት ሰርስረው ለስርቆት ይገባሉ፤ ቀን ግን ተሸሽገው ይውላሉ። ብርሃንንም ይጠላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጨለማ ቤቶችን ይነድላል፤ በቀን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንንም አያዩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቶቹን በጨለማ ይነድላሉ፥ በቀን ይሸሸጋሉ፥ ብርሃንም አያውቁም። |
በመካከላቸውም ያለው ልዑል በትከሻው ላይ ተሸክሞ በጨለማ ይወጣል፥ በዚያም ሊወጡ ግንቡን ይቦረቡራሉ፥ በዓይኑም ምድሪቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።
“ነገር ግን ይህን እወቁ፤ ባለቤት ሌባ ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ ነቅቶ በጠበቀ ነበር፤ ቤቱም እንዲቆፈር ባልተወም ነበር።