ኢዮብ 24:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአመንዝራ ሰው ዐይን ጨለማን ይጠብቃል፦ የማንም ዐይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አመንዝራ በዐይኑ ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤ ‘ማንም አያየኝም’ ብሎ ያስባል፤ ፊቱንም ይሸፍናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አመንዝራ ሰው የቀኑን መምሸት ይጠባበቃል፤ ማንም ሰው እንዳያየው ፊቱን ይሸፍናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአመንዝራም ዐይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፦ የማንም ዐይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፦ የማንም ዓይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል። |
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።