ኢዮብ 24:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሰ ገዳዩም ሳይነጋ ማልዶ ይነሣል፥ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፥ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኑ ሲመሽ፣ ነፍሰ ገዳይ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድኾችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ያደባል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፍሰ ገዳይ ገና ሳይነጋ በማለዳ ተነሥቶ፥ ድኾችንና ችግረኞችን ይገድላል፤ በሌሊትም ለስርቆት ይሰማራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራቸውንም ዐውቆ ለጨለማ ዳረጋቸው። በሌሊትም እንደ ሌባ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሰ ገዳዩም ሳይነጋ ማልዶ ይነሣል፥ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፥ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው። |
ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤
እንግዲህ ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንደምመጣብህ ከቶ አታውቅም።