ኢዮብ 24:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፥ ተርበው ነዶዎችን ይሸከማሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ይሄዳሉ፤ ነዶ ይሸከማሉ፤ ግን ይራባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድኾች ምንም ልብስ ሳይኖራቸው ራቁታቸውን ወደ ሥራ ይሰማራሉ። በመከር ወራት ነዶ ተሸክመው እያጋዙ እነርሱ ይራባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ችግረኞችን በደሉአቸው፥ ጣሉአቸውም፤ ከተራቡትም የሚጐርሱትን ነጠቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፥ ተርበው ነዶዎችን ይሸከማሉ፥ |
“የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፥ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።