የሚመልስልኝም ቃል ምን እንደሆነ አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም አስተውል ነበር።
የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደ ሆነ ባወቅሁ ነበር፤ የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።
የሚሰጠኝን መልስ ዐውቅ ነበር፤ ምን እንደሚለኝም እረዳ ነበር።
የሚሰጠኝንም ፈውስ አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም አስተውል ነበር።
የሚመልስልኝም ቃል ምን እንደ ሆነ አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም አስተውል ነበር።
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ።
በፊቱ አቤቱታዬን አቀርብ ነበር፥ አፌንም በማስረጃ እሞላው ነበር።
በታላቅ ኃይሉ ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? ይልቁንም! ማዳመጥ ይበቃው ነበር።