ኢዮብ 22:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞልቶት ነበር፥ የክፉ ሰው ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤታቸውን በመልካም ነገር የሞላው ግን እርሱ ነው፤ ስለዚህ ከኀጢአተኞች ምድር እርቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ቤታቸውን በብልጽግና የሞላው እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እኔ የክፉ ሰዎችን ሐሳብ አልቀበልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፤ የኃጥኣን ምክር ከእርሱ የራቀች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፥ የኃጥአን ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት። |
አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”