ኢዮብ 22:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም፦ “እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሆኖ ሳለ እንዲህ አልህ፤ ‘እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በእንዲህ ያለ ጨለማ ውስጥስ ይፈርዳልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን ‘እግዚአብሔር ምን ያውቃል? ከድቅድቅ ጨለማ ባሻገር ሆኖ እንዴት ሊፈርድብን ይችላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም እንዲህ ብለሃል፦ ኀያል እርሱ ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም፦ እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን? |
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።
በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤
በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ በአተላቸውም ላይ የሚረጉትን፥ በልባቸውም፦ “ጌታ መልካምም ክፉም አያደርግም” የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።