ኢዮብ 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናመልከውስ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወይስ ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ይጠቅመናል?” ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እናመልከው ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ማነው? ወደ እርሱስ መጸለይ ምን ይጠቅመናል?’ ይላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንገዛለትስ ዘንድ እርሱ ምን ይችላል? ወይስ ወደ እርሱ ብንቀርብ ምን ይጠቅመናል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናመልከውስ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወይስ ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ይጠቅመናል? ይላሉ። |
በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ።
እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙን መጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ ፊት ኀዘንተኞች ሆነን መሄድ ምን ይጠቅመናል?