ኢዮብ 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፥ እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምግቡ በሆዱ ውስጥ ይመርራል፤ በውስጡም እንደ እባብ መርዝ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሆዱ ውስጥ ግን ወደ መራራነት ይለወጣል፤ እንደ እባብ መርዝም ይሆንበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጽሞ ራሱን መርዳት አይችልም። የእፉኝትም መርዝ ከከንፈሩ በታች አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፥ እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል። |
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”