አዳምንም አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም ከእርሱ በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርሷ ትበላለህ፤
ኢዮብ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን፦ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፥ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን?” አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደ ሞኝ ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፤ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።” በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮብም “እንዴት የሞኝ ሴት ንግግር ትናገሪያለሽ? እግዚአብሔር መልካም ነገር ሲሰጠን በደስታ እንቀበላለን፤ ታዲያ፥ መከራ ሲያመጣብን በእርሱ ላይ ማጒረምረም ይገባናልን?” አላት። ኢዮብ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ መከራና ሥቃይ ቢደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ነገር በመናገር ኃጢአት አልሠራም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፥ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን? አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም። |
አዳምንም አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም ከእርሱ በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርሷ ትበላለህ፤
እኔስ እንዴት እሆናለሁ? ነውሬንስ ተሸክሜ የት እገባለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል ከወራዳዎቹ እንደ አንዱ ትቆጠራለህ፤ እባክህ ለንጉሡ ጠይቀው፤ እኔንም አይከለክልህም።”
በጌታዬ በንጉሡ ፊትም የእኔን የአገልጋይህን ስም አጥፍቶአል፤ ንጉሥ ጌታዬ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆንህ ደስ ያሰኘህን አድርግ።
ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።
ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”
በመልካም ቀን ደስ ይበልህ፥ በክፉም ቀን ተመልከት፥ ሰው ከእርሱ በኋላ መርምሮ ምንም እንዳያገኝ እግዚአብሔር ይህንንም ያንንም እንዲሁ ሠርቶአል።