ኢዮብ 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤ መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሐዘን የተነሣ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ መላ ሰውነቴም እንደ ጥላ ሆኖአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኖች ከእንባ የተነሣ ፈዘዙ፥ ሁሉም እጅግ ተጸየፉኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ ብልቶቼም ሁሉ እንደ ጥላ ሆኑ። |
ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?